The Impacts of Peer Corrections versus Teachers' Corrections on Students’ Writing Performance

Authors

  • Ephriem Tiruneh University of Gondar

Keywords:

የመምህር እርማት, የግለ-ቢጤ እርማት

Abstract

The general objective of this research was to probe the role of self-peer correction versus teacher correction on students’ writing performance. To achieve this objective, grade 9th students of Fasiledes Secondary School were selected by purposive sampling technique. Data was collected using pre and post writing essays test, observation and interview. The data from pre and post writing essay tests were analyzed using descriptive and inferential (independent sample t-test) statistics; the observation and interview data were also analyzed qualitatively. The result of this study revealed that there was significant difference (p=00) between the mean scores of the two groups (self-peer versus teacher) for the post writing essay test. This indicated that teachers’ correction had strong effect on students writing performance than self-peer correction. Moreover, the feedback given by peers was found to be unconstructive and less helpful and hence students prefer teacher’s correction than selfpeer correction. Therefore, the researcher suggests that students’ writing can be improved if teachers give accurate and appropriate feedback in a writing lesson. 

የዚህ ጥናት ዐቢይ ዓላማ የመጻፍ ክሂልን በማስተማር ሂደት የግለ-ቢጤ እርማትና የመምህር እርማት ስልት የተማሪዎችን ድርሰት የመጻፍ ችሎታ ለማሻሻል ያላቸውን አስተዋጽኦ መፈተሽ ነው፡፡ ይህን ዓላማ ለማሳካትም በጎንደር ከተማ የፋሲለደስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአመቺ ናሙና ተመርጧል፡፡ በዚህ ትምህርት ቤት በ2010 ዓ.ም. ተመዝግበው የዘጠነኛ ክፍል ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ተማሪዎች በዓላማ ተኮር ናሙና ተመርጠዋል፡፡ መረጃዎቹ በቅድመና ድህረ ልምምድ የድርሰት ፈተናዎች፣ በምልከታና በቃለመጠይቅ ተሰብስበዋል፡፡ የተሰበሰቡት መረጃዎች እንደአግባብነታቸው በመጠናዊና በዓይነታዊ የመተንተኛ ዘዴዎች ተተንትነዋል፡፡ ዓይነታዊ መረጃዎች በሐተታ ሲገለጹ፣ መጠናዊ መረጃዎቹ ደግሞ በገላጭና በድምዳሜያዊ ስታትስቲክስ (በነፃ ናሙናዎች ቲቴስት) በመጠቀም ተተንትነዋል፡፡ በውጤት ትንተናው መሠረትም በግለ- ቢጤ እርማት ስልት የተለማመዱት ድህረ ልምምድ የድርሰት ፈተና አማካይ ውጤት በመምህር እርማት ስልት ከተለማመዱት የድርሰት ፈተና አማካይ ውጤት አንሶ ጉልህ ልዩነት (P=0.000) አሳይቷል፡፡ በመሆኑም የግለ-ቢጤ እርማትን ከተጠቀሙት ተማሪዎች ይልቅ የመምህር እርማት ያገኙ ተማሪዎች ድርሰት መሻሻል እንደታየበት የውጤት ትንተናው አመላክቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት የተማሪዎቹን ድርሰት የመጻፍ ችሎታ በማጎልበት ረገድ የመምህር እርማት ውጤታማ እንደሆነ የጥናቱ ውጤት ጠቁሟል፡ ፡ ከዚህ በተጨማሪ ተማሪዎቹ ለቢጤዎቻቸው ድርሰት የሚሰጡት ምጋቤ ምላሽ በሳል እንዳልሆነ የጥናቱ ውጤት አሳይቷል፡፡ በመጨረሻም ድርሰትን ከግለ-ቢጤ እርማት እና ከመምህር እርማት ስልት አንጻር የተማሪዎች ምርጫ የመምህር እርማት እንደሆነ የጥናቱ ውጤት አመላክቷል፡፡ ስለሆነም መምህራን በክፍል ውስጥ በትክክል ተገቢ እርማት መስጠት ከቻሉ የተማሪዎች ድርሰት የመጻፍ ችሎታ እንደሚሻሻል አጥኚው ይጠቁማል፡፡

Downloads

Published

2020-07-01

How to Cite

Ephriem Tiruneh. (2020). The Impacts of Peer Corrections versus Teachers’ Corrections on Students’ Writing Performance. Ethiopian Renaissance Journal of Social Sciences and the Humanities, 7(1), 81–92. Retrieved from https://erjssh.uog.edu.et/index.php/ERJSSH/article/view/148